አየር መንገዱ በ22 የመንገደኛ አውሮፕላኖቹ ላይ የምህንድስና ማስተካከያ አደረገ

3 Yrs Ago
አየር መንገዱ በ22 የመንገደኛ አውሮፕላኖቹ ላይ የምህንድስና ማስተካከያ አደረገ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮቪድ-19 ያሳደረውን ጫና ለመቋቋም አዲስ ስትራቴጂ በመጠቀም ተጨማሪ 22 የመንገደኛ አውሮፕላኖችን የጭነት አገልግሎት እንዲሰጡ በውስጥ አቅም የምህንድስና ማስተካከያ በማድረግ ሥራ መጀመሩን አስታውቋል።

በወረርሽኙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የመንገደኛ በረራዎቹን ከ90 በመቶ በላይ እንዲቆሙ በመደረጋቸው የአየር መንገዱን ህልውና የሚፈታተንና ከአለም አቀፋዊ ቀውሱ ለመውጣት የስራቴጂክ እቅድ ለውጥ በማድረግ የትኩረት አቅጣጫውን ወደ እቃ ጭነት ቢዝነስ በማዞር እየሰራ እየሰራ መሆኑም ተገልጿል።

አየር መንገዱ በመላው አለም እየጨመረ ለመጣው የጭነት አገልግሎት ፍላጎት በነበሩት የጭነት ማመላለሻ አውሮፕላኖች አጠናክሮ አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱም ነው የተገለፀው።

በመንገደኛ አውሮፕላኖቹ ውስጥ የሚገኙ መቀመጫዎች ለጭነት አገልግሎት እንዲውሉ የተሰራው አለማቀፍ የአቪየሽንና የቴክኒክ ተቆጣጣሪ አካላት ያስቀመጧቸውን መስፈርቶች በመከተልና በማሟላት እንደሆነም ገልጿል።

አየር መንገዱ የኮሮናን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ህይወት አድን የሆኑ የህክምና ቁሳቁሶችን በመላው አፍሪካ በማጓጓዝ ላይ ነው።

የአገልግሎት ተልእኮውን በብቃት ለመወጣትም በመንገደኛ አውሮፕላን የእቃ ማስቀመጫ ቦታ፣ እንዲሁም የአውሮፕላኖቹ ወንበሮች ሳይነሱ ጭነት በመጫን አገልግሎቱን እየሰጠ እንደሆነ እና ይህ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የአየር መንገዱ ባለሞያዎች በዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ምስጋና እንደቀረበላቸው ኢዜአ አስታውቋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top