የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላት ችግኝ ተከሉ

3 Yrs Ago
የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላት ችግኝ ተከሉ

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን በዛሬው እለት በየካ ክፍለ ከተማ ሚሊኒየም ፓርክ ችግኝ ተክለዋል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባል ቤተ እምነቶች በሙሉ በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ተካፋይ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጋር በመተባበር በተካሄደው መርሃ ግብር ከ2 ሺህ 500 በላይ ችግኞች ተተክለዋል።

https://www.facebook.com/EBCzena/photos/pcb.3406688282696357/3406769522688233/?type=3&theater

ዛሬ ላይ የምንተክላቸው እፅዋት ዘር፣ ጎሳና ሃይማኖት ሳይለዩ የሚያገለግሉ በመሆናቸው ሁላችንም አንድነታችንን የምናሳይባቸው በመሆናቸው ህብረተሰቡ ሊሳተፍበት እንደሚገባ የእምነት አባቶች አሳስበዋል።

መትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብም ያስፈልጋል ነው የእምነት አባቶቹ ያሉት።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብም ከጫፍ እንዲደርስ አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችን ማድረግ እንደሚገባም ተገልጿል።

ሪፖርተር፡- ብሩክ ተስፋዬ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top