የኮይሻ፣ ወንጪ እና ጎርጎራ የልማት ፕሮጀክቶች የገቢ ማሰባሰቢያ እንቅስቃሴ እየተገመገመ ነው

3 Yrs Ago
የኮይሻ፣ ወንጪ እና ጎርጎራ የልማት ፕሮጀክቶች የገቢ ማሰባሰቢያ እንቅስቃሴ እየተገመገመ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኮይሻ፣ ወንጪ እና ጎርጎራ የልማት ፕሮጀክቶች የሚካሄደውን የገቢ ማሰባሰቢያ እንቅስቃሴ ለመገምገም ከገበታ ለሀገር አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ተገናኝተዋል። 

የመንግሥት ሠራተኞች የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለዚሁ ተግባር ለግሰዋል።  በውጪ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በውጪ ምንዛሬ የባንክ ሂሳቦች ድጋፋቸውን የሚያስገቡ ሲሆን፣ በንግዱ ማኅበረሰብ አስቀድሞ ቃል የተገባውን ጨምሮ፣ ቀጣይ የገቢ ማሰባሰቢያ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው ቀጥለው የታሰበውን የ3 ቢሊየን ብር ድጋፍ የሚያስገኙ እንደሚሆኑ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top