ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የፌደራል ተቋማት የ100 ቀናት አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በህዳሴው ግድብ በመካሄድ ላይ ነው

2 Yrs Ago
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የፌደራል ተቋማት የ100 ቀናት አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በህዳሴው ግድብ በመካሄድ ላይ ነው
 
 
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የካቢኔ የፌደራል ተቋማት የ100 ቀናት አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
ላለፉት ሳምንታት የተቋማቱን አፈጻጸም በተለያየ የቁጥጥር ስርዓቶች ሲከታተል የቆየው የፕላንና ልማት ሚንስቴርም የእያንዳንዱን ሚንስቴር ተቋማት አፈጻጸምን በመድረኩ አቅርቧል፡፡
ሚንስትሯ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) እንዳሉት ሀገሪቱ ባስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ብታልፍም ባለፉት 100 ቀናት በዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፎች ጥሩ ውጤት ተመዝግቧል።
ባለፉት 100 ቀናት በግብርናው ዘርፍ የመኸር ምርት መሰብሰብ እና የመስኖ ዝግጅት ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።
ከወጪ ንግድም በ100 ቀናት ውስጥ ከ800 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱንም የፕላንእና ልማት ሚንስትሯ ባቀረቡት ሪፓርት ገልጸዋል ።
ኢኮኖሚው በማክሮ ደረጃ ጥሩ ውጤት እንደተመዘገበት ቢገመገምም ሀገሪቱ ተገዳ በገባችበት ጦርነት ምክንያት ከፊቱ በርካታ ፈተናዎች እንደተደቀኑበት ሚንስትሯ በግምገማ መድረኩ ላይ ተናግረዋል።
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የተጀመረው የፌደራል ተቋማትን የሚመሩት ሚንስትሮች ስብሰባ ሁልጊዜ ከሚካሄድበት የጠቅላይሚንስትር ጽ/ቤት ወጣ ብሎ ሲካሄድ ይህ ለሁለተኛ ጊዜው ነው።
ከዚህ በፊት በኮይሻ መካሄዱም የሚታወስ ነው።
በአስማማው አየነው(ከጉባ)

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top