"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከፕሬዝዳንት ባይደን ጋር ያደረጉት ውይይት በዲፕሎማሲው አውድ መሻሻሎች የመኖራቸው ማሳያ ነው" - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

2 Yrs Ago
"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከፕሬዝዳንት ባይደን ጋር ያደረጉት ውይይት በዲፕሎማሲው አውድ መሻሻሎች የመኖራቸው ማሳያ ነው" - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር ያደረጉት የስልክ ውይይት ከዚህ ቀደም የነበረው የግንኙነት መንፈስ እየተቀየረ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለሕግ ማስከበር ዘመቻው ለፕሬዝዳንቱ እንዳብራሩላቸው የገለፁት አምባሳደር ዲና፥ መሪዎቹ በውይይታቸው ከሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ ከሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት እና በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ከማቋቋም ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ማንሳታቸውን ጠቅሰዋል።

ከዚህ ቀደም የተስተዋለውን በጥርጣሬ የተቃኘ አካሄድ ለመለወጥ ለንግግር ዝግጁ መሆናቸውን ማሳየታቸውን እና በጋራ ጉዳዮች ላይ አብረው ለመስራት መስማማታቸውን ገልፀዋል።

በዚህም የፓለቲካ ዲፕሎማሲ ምህዳሩ መንፈስ እየተቀየረ መምጣቱ ታይቷልም ነው ያሉት፡፡

ውይይቱ ግንኙነትን በማጠናከር ረገድም ውጤታማ ስራ እንዲሰራ መንገድ የሚከፍት መሆኑን አምባሳደር ዲና መናገራቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

በአንድ በኩል የሕልውና አደጋውን ለመቀልበስ በተደረገው ዘመቻ የተገኘው ድል፣ በሌላ በኩል ብሄራዊ መግባባትን ለማምጣት የተጀመረው ሂደት በኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የበረታ ትግል የእስካሁኑ ጫና ትርጉም እንዲያጣ ሆኗል ብለዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top