የአሁኑ ትውልድ ጊዜው በሚጠይቀው አርበኝነት የራሱን ታሪካዊ ኃላፊነት ሊወጣ ይገባል፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

1 Yr Ago
የአሁኑ ትውልድ ጊዜው በሚጠይቀው አርበኝነት የራሱን ታሪካዊ ኃላፊነት ሊወጣ ይገባል፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
የአሁኑ ትውልድ ጊዜው የሚጠይቀውን የአርበኝነት ሥራ በመሥራት የራሱን ታሪካዊ ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳሰበ።
ምክር ቤቱ 81ኛው የኢትዮጵያውያን አርበኞች የድል በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፏል።
በመልእክቱም፣ ሀገር በየጊዜው በሚፈጠሩ ጀግኖቿ እና አርበኞች ልጆቿ አንድነቷ ፀንቶ፣ ነፃነቷ ተጠብቆ እና ዳር ድንበሯ ተከብሮ በትውልድ ቅብብሎሽ ከዚህ መድረሷን ጥቅሷል።
አዲሱ ትውልድም የእናት አባቶቹ ታሪክ ወራሽ ትውልድ ብቻ ሳይሆን የራሱን ታሪክ በመሥራት ሀገራችን ኢትዮጵያ የበለፀገች፣ ማኅበራዊ ፍትሕ የሰፈነባት እና እውነተኛ ዴሞክራሲ የሚተገበርባት ሀገር እንድትሆን ሁሉም ዜጋ በተሰማራበት የሥራ መስክ ሁሉ ለሀገር ክብር እና ጥቅም የልማት አርበኛ ሊሆን ይገባል ሲል አሳስቧል።
እናቶቻችን እና አባቶቻችን ጊዜው የሚጠይቀውን የሕይወት መሥዋዕትነት በመክፈል ጭምር ነፃነቷ እና አንድነቷ የተጠበቀ ሀገር አውርሰውናል ያለው ምክር ቤቱ፣ እኛም ዘመኑ የሚጠይቀውን መሥዋዕትነት በመክፈል ከድህነት የወጣች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ ለማስረከብ ተግተን መሥራት ይኖርብናል ሲል መልእክቱን አስተላልፏል።
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top