ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

1 Yr Ago
ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ
ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ በጋራ ለመሥራት በሚያስችላቸው ዝርዝር ተግባራት ላይ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ ሁለቱ ሀገራት በባዮ ቴክኖሎጂ፣ በህዋ ሳይንስ እና በዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ያስችላቸዋል።
እስከ 2025 (እ.አ.አ) የሚቆየው ይህ የትብብር ስምምነት የሰው ኃይል ሥልጠና፣ የባለሙያ ልውውጥ፣ በኢኖቬሽን ‘ስታርትአፕ’ እና በሌሎች የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፎች ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
መስከረም ወር ላይ የተቋቋመው የሁለቱ ሀገራት የቴክኒክ ኮሚቴ ያዘጋጀውን የትብብሩን ዝርዝር ተግባራት ስምምነት በኢትየጵያ በኩል የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ፒ.ኤች.ዲ) እና በደቡብ አፍሪካ በኩል ድግሞ የሳይንስ እና ኢኖቬሽን ዲፓርትመንት ተወካይ ሚስተር ዳን ዱ ቶይት ፈርመወታል።
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ፒ.ኤች.ዲ) ኢትዮጵያ በህዋ ሳይንስ፣ በምርምር እና በዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ ደቡብ አፍሪካ ያላትን የተሻለ ልምድ ትወስዳለች ማለታቸውን ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top