ሶስት የመንግስት ተቋማት የግንባታ ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት በጋራ ለመስራት ተስማሙ

1 Yr Ago
ሶስት የመንግስት ተቋማት የግንባታ ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት በጋራ ለመስራት ተስማሙ
 
ሶስት የመንግስት ተቋማት የግንባታ ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት በጋራ ለመስራት ተስማሙ
 
ከውጭ የሚገቡ የግንባታ ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት ሶስት የመንግስት ተቋማት በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
የመግባቢያ ስምምነቱን የተፈራረሙት የከተማና መሠረተልማት ሚኒስቴር፣ ማዕድን ሚኒስቴር እና የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ናቸው።
የከተማና መሠረተ ልማት ሚንስትሯ ጫልቱ ሳኒ፤ የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ስምምነቱን ተፈራርመዋል።
የስምምነቱ ዋነኛ ዓላማም ከውጭ የሚገቡ የግንባታ ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት በጋራ ለመስራት መሆኑ ተገልጿል።
በኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የግንባታ ዘርፍ ለማገዝ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚገቡ የግንባታ እቃዎችን በሀገር ውስጥ መተካት ያስፈልጋል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።
ለኮንስትራክሽን ዘርፉ እድገት በቅንጅት ለመስራት የተቋማቱ የጋራ ስምምነት ወሳኝ ሲሆን የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ምረት ለመተካትም ጉልህ ጠቀሜታ አለው ተብሏል።
 
 
የሐረሪ ብሔረሰብ የሸዋል ዒድ በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው
********************
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top