ኢትዮጵያ ለዓለም እና ለቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች"፦ ዶ/ር አብርሀም በላይ

1 Yr Ago
ኢትዮጵያ ለዓለም እና ለቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች"፦ ዶ/ር አብርሀም በላይ
ኢትዮጵያ ለዓለም እና ለቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሀም በላይ ገለጹ። በቻይና አዘጋጅነት በተካሄደው የቻይና-አፍሪካ የሚኒስትሮች የሰላም እና የፀጥታ ፎረም ላይ በመሳተፍ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ዶ/ር አብርሀም በላይ፣ ወቅቱ በዓለማችንም ሆነ በአካባቢያችን የሚታዩ የፀጥታ ችግሮችን ለመቅረፍ ከሰላም ኃይሎች ጋር በትብብር መሥራት የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው ብለዋል። የቀደምት ሥልጣኔ ባለቤት የሆነችው ሀገራችን ኢትዮጵያም በፓን-አፍሪካን መንፈስ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካውያን ለመፍታት እንዲቻል በፅናት እየሠራች መሆኗን ጠቁመው፣ የቻይና ሪፐብሊክ መንግሥትም አካታች እና ሚዛናዊ አካሄድን በመከተል ለዓለም ሰላም እና መረጋጋት እያደረገ ላለው ሚና ያላቸውን ክብር እና አድናቆት መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። “የጋራ ደህንነትን ለማረጋገጥ አብሮነት እና ቅንጅትን ማጠናከር ይገባል፤” በሚል መርሕ በተካሄደው ሁለተኛው የቻይና-አፍሪካ የሚኒስትሮች የሰላም እና የፀጥታ ፎረም ከሃምሣ በላይ ሚኒስትሮች እና የአፍሪካ ኅብረት ተወካዮች ተሳትፈዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top