በትምህርት የታነፀ ዜጋን ለመፍጠር የትምህርቱን ተግባር በቅንጅት መምራት ይገባል”፦ ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ

1 Yr Ago
በትምህርት የታነፀ ዜጋን ለመፍጠር የትምህርቱን ተግባር በቅንጅት መምራት ይገባል”፦ ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ
በትምህርት የታነፀ እና በዕውቀት የተገነባ ዜጋን ለመፍጠር የትምህርቱን ተግባር በቅንጅት መምራት እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ ተናገሩ። በመላው የኅብረተሰብ ተሳትፎ የትምህርት ልማት ዕቅዶችን እናሣካለን!” በሚል መሪ ቃል የክልሉ የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም፣ የ2015 መሪ ዕቅድ እና የ2015 የትምህርት ዘመን ክልላዊ የትምህርት ንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ፣ “ያለበቂ ዕውቀት የሚመሩ ተግባራት በቂ እና አስተማማኝ ውጤት አያስመዘግቡም፣ ለዚህም የትምህርቱ ዘርፍ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል” ብለዋል።
ሥራው ውስብስብ ሂደቶችን የሚያልፍ እንደመሆኑ የትምህርት ልማት ሥራዎች በዕውቀት በተካኑ የትምህርት አመራር መመራት እንደሚገባ ተናግረዋል። ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ፣ በ2014 በጀት ዓመት ጀምሮ በክልሉ አዲሱ የፍኖታ ካርታ ተግባራዊ በማድረግ እየተሠራ እንደሆነ ተናግረዋል። በመድረኩ የ2014 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት እየቀረበ የሚገኝ ሲሆን የ2015 መሪ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎ የግብ ስምምነት የመፈራረም እና የንቅናቄው ማጠቃለያ የሥራ መመሪያ እና ቀጣይ አቅጣጫዎች እንደሚቀመጥ የሚቀመጥ መሆኑን ከክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top