በአሸባሪው ሸኔ ላይ እየተወሰደ ባለው እርምጃ ስኬት ተመዝግቧል" - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

1 Yr Ago
በአሸባሪው ሸኔ ላይ እየተወሰደ ባለው እርምጃ ስኬት ተመዝግቧል" - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
የተጠና እርምጃ በመውሰድ በአሸባሪው ሸኔ ላይ ከባድ ኪሳራ ማድረስ መቻሉን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም፥ የአሸባሪው ሸኔን ጥቃት የመከላከልና ቡድኑን የማስወገድ ዘመቻ ሲካሄድ መቆየቱን አንስተዋል። የሽብር ቡድኑ በተለይ በኦሮሚያ ክልልና አዋሳኝ አካባቢዎች ጥቃት ሲያደርስ መቆየቱን አስታውሰው፥ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በፌዴራልና ኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ኃይሎች ጥምረት በቡድኑ ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን እና በዚህም ስኬት መመዝገቡን ገልጸዋል። እርምጃው የሽብር ቡድኑን እንቅስቃሴ ከግምት ውስጥ በማስገባት በተጠኑ አካባቢዎች የተወሰኑ ቦታዎችን ዒላማ በማድረግ መከናወኑን አመልክተዋል። ለአብነትም ከጥቂት ቀናት በፊት በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን፣ ሱሉላ ፊንጫ ወረዳ በተከናወነ የተቀናጀ ኦፕሬሽን በበርካታ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን አንስተዋል። በተወሰደው እርምጃ በርካታ የጦር መሳሪያዎችና የመገናኛ ሬዲዮዎች መያዛቸው ተገልጿል። የሽብር ቡድኑ የተለያዩ ግብዓቶችን ሲያከማችባቸው የነበሩ 69 መጋዝኖችም ከጥቅም ውጭ እንዲሆኑ ተደርጓል ነው ያሉት። ከሐምሌ 16 እስከ ሐምሌ 22 በተካሄደ የተቀናጀ ዘመቻ 333 በሚሆኑ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታዋ፥ አሸባሪውን ቡድን እያገዙ ነው በሚል የተጠረጠሩ 671 ግለሰቦችም በሕግ ቁጥጥር ስር ሆነው ጉዳያቸው እየተጣራ ይገኛል ነው ያሉት። በፌዴራልና ኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ኃይሎች ቅንጅት እየተካሄደ ባለው ፀረ-ሸኔ ዘመቻ የህብረተሰቡ ቀጥተኛ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ አንስተው፥ ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር የቡድኑን ተልዕኮ በማክሸፉ ጥረት ላይ እንዲሳተፍና እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል።
 
 
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
 

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሙሉ መግለጫ 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top