የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ10 ወራት ውስጥ ተልዕኮውን በብቃት መከወን ጀምሯል" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

1 Yr Ago
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ10 ወራት ውስጥ ተልዕኮውን በብቃት መከወን ጀምሯል" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጋር በመሆን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መስሪያ ቤትን ጎብኝተው ከሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል ጋር ተወያይተዋል። በቅርቡ የተቋቋመ ተቋም እንደ መሆኑ፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ10 ወራት ውስጥ ብቻ በሚያስደንቅ ሁኔታ ራሱን አዋቅሮ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሥራና ክህሎትን የመፍጠር ተልዕኮውን በብቃት መከወን ጀምሯል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጉብኝቱ በኋላ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት አስተያየት። የሥራ ዕድልን ማመቻቸት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚስትሩ፤ ይህንኑ የሚያሳልጥ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የተቋቋመው የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግዳሮቶችን በብቃት ለመወጣት እንዲሁም የሠለጠነ የሰው ኃይልና የአገልጋይነት አመለካከት ያላቸውን አገልጋዮች ለማብቃት እንዲቻል ነው ሲሉ አብራርተዋል። የሥራ ዕድል ፈጠራን በበቂ ሁኔታ ለማመቻቸት፣ መሥሪያ ቤቱ ያለው ብቃት ሊጠናከርና ሊፋጠን ያስፈልጋልም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ።
 
 
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top