የአሸባሪው ሸኔ የደቡብ ዞን ምክትል ሀላፊ በቁጥጥር ስር ዋለ

1 Yr Ago
የአሸባሪው ሸኔ የደቡብ ዞን ምክትል ሀላፊ በቁጥጥር ስር ዋለ
በአሸባሪው ሸኔ የደቡብ ዞን ምክትል ሀላፊ የሚል ሀላፊነት የተሰጠው ተጠርጣሪ በቤት መኪና ወደ መሀል አገር ሲጓዝ በቦረና ዞን ሞያሌ ወረዳ መያዙን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ገለጸ፡፡ የመምሪያው ኮሚኒኬሽን ረዳት ዲቪዥን ሀላፊ ኢንስፔክተር ግርማ ሹሚ ተጠርጣሪው ከአዳማ ከተማ በተላከለት የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 B-37253 አአ በሆነ መኪና በመጓዝ ላይ እንዳለ በፖሊስ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰአት አከባቢ መያዙን ተናግረዋል፡፡ በቁጥጥር ስር የዋለው ተጠርጣሪ ቀድሞ የሚታወቅበትን ‘መሀመድ አሜ’ የሚለውን የመጠሪያ ስሙን አብዱ ኡመር ሁሴን በሚል ቀይሮ መታወቂያ በማሰራት ሲንቀሳቀስ እንደነበር መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ግለሰቡ ከአሸባሪው የሸኔ ቡድን ጋር ብቻ ሳይሆን አልሻባብን ከመሳሰሉ ከአለም አቀፍ አሸባሪዎች ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚጠረጠር እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ የቦረና ዞን ፖሊስ ተጠርጣሪውን ጭኖ የነበረውን መኪና ከነአሽከርካሪው በቁጥጥር ስር አውሎ ጉዳዩን በመከታተል ላይ እንደሆነ ገልጸዋል፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top