ባለፉት 6 ወራት ከ500 ሺህ በላይ ዓለም አቀፍ ቱሪስቶች ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል:- የቱሪዝም ሚኒስቴር

1 Yr Ago
ባለፉት 6 ወራት ከ500 ሺህ በላይ ዓለም አቀፍ ቱሪስቶች ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል:- የቱሪዝም ሚኒስቴር
ባለፉት 6 ወራት ከ500 ሺህ በላይ ዓለም አቀፍ ቱሪስቶች ኢትዮጵያን መጎብኘታቸውን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።
ቱሪስቶቹ በተለያየ ምክንያት ወደ ሃገሪቱ የሚመጡት እና ሆነ ብለው አቅደው ሃገሪቱን ለመጎብኘት የሚመጡትን ቱሪስቶች እንደሚያጠቃልል በቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም መዳረሻ ልማት ዳይሬክተር አቶ ሙሳ ከድር በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር ተናግረዋል።
ከኮቪድ እና ከጦርነቱ በኋላ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ቱሪዝሙ ቀስ በቀስ እንዲያንሰራራ ተደርጓል ያሉት አቶ ሙሳ፣ አሁን ላይ የቱሪዝሙ እንቅስቃሴ መሻሻል እያሳየ እንደመጣ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በብዛት የምታስጎበኛቸው መስህቦች ያሉት በሰሜኑ አካባቢ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በአካባቢው ተከስቶ የነበረው ግጭት ቱሪዝሙ እንዲዳከም የራሱ አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል አቶ ሙሳ።
ባለፉት ወራቶች በተለያዩ ፌስቲቫሎች ለመሳተፍ ማለትም በመስቀል፣ በገና፣ በጥምቀት ብዛት ያላቸው የዓለም አቀፍ እና የአገር አቀፍ ቱሪስቶች ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ መጎብኘታቸውን ነው አቶ ሙሳ የገለጹት።
ከዚህ በፊት ቱሪዝም በመንግስት ደረጃ የማህበራዊ ዘርፍ ተደርጎ ነበር የሚወሰደው፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የአገር በቀል የኢኮኖሚ ዘርፎች ማሻሻያ በተደረገ ጊዜ ቱሪዝም አንዱ የድህነት ቅነሳ ኢኮኖሚ ዘርፍ ሆኖ እውቅና ተሰጥቶት በ4ኛ ደረጃ እንደሚገኝ አቶ ሙሳ ጠቁመዋል።
ቱሪዝም በመንግስት ደረጃ ከቀዳሚዎች የኢኮኖሚ ዘርፎች አንዱ መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው፣ ይህንን ፍላጎት ከግብ ለማድረስ ግን ትልቁ ተግዳሮት የመሰረተ ልማት እና የአገልግሎት አቅርቦት ችግር እንደሆነ አቶ ሙሳ ጠቁመዋል።
በመስፍን ገብረማርያም

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top