ቻይና ወሳኝ በተባሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ዓለምን መምራት ጀምራለች፦ ሪፖርት

1 Yr Ago
ቻይና ወሳኝ በተባሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ዓለምን መምራት ጀምራለች፦ ሪፖርት
ቻይና ወሳኝ በተባሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ዓለምን መምራት መጀመሯን የአውስትራሊያው የስትራቴጂክ ፖሊሲ ጥናቶች ኢንስቲትዩት ባወጣው ሪፖርት ጠቆመ።
ተቋሙ ባወጣው ሪፖርት ቻይና ከ44 ቁልፍ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ውስጥ በ37ቱ ከምዕራባዊያኑ ቀዳሚ ደረጃን መያዟን አረጋግጧል።
ሰው ሠራሽ አስተውሎ፣ የኤሌክትሪክ ባትሪ፣ ሰው አልባ አውሮፕላን፣ የኑክሌር ኃይል፣ የሮቦት ሳይንስ እና የሕዋ ምርምር ቻይና ከፍተኛ ዕድገት ያሳየችባቸው የቴክኖሎጂ ዘርፎች ናቸው ተብሏል።
ሀገሪቱ በመከላከያ፣ በጠፈር፣ በሮቦቲክስ፣ በኢነርጂ፣ በከባቢያዊ፣ በባዮቴክኖሎጂ፣ በሰው ሠራሽ አስተውሎ፣ በላቁ ቁሶች እና በቁልፍ የኳንተም ቴክኖሎጂዎች ቀድሞውኑም የበላይነት የያዘች ዚሆን በዓለም ቀዳሚ የቴክኖሎጂ ልዕለ ኃያል የመሆን ቁመና ላይ እንዳለች የአውስትራሊያ ስትራቴጂክ ፖሊሲ ኢንስቲትዩት በሪፖርቱ ጠቁሟል።
በሳይንሳዊ ምርምር ስመ-ጥር የሆኑ 10 ተቋማት ሁሉም ቻይና ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውም ተገልጿል።
አሜሪካ እና አውሮፓ በወሳኝ የቴክኖሎጂ ዘርፎች በቻይና እየተቀደሙ መሆናቸውን ይኸው የአውስትራሊያ የፖሊሲ ምርምር ተቋም አሳውቋል።
ቻይና አሁን ላይ በሚታወቁ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ብቻ ሳይሆን ወደፊት በሚፈጠሩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችም የበላይነት ለመያዝ ሩቅ አሳቢ ዕቅድ እንዳላትም ተገልጿል።
የቻይና ግስጋሴም ሀገሪቱን በቅርቡ የቴክኖሎጂ ልዕለ-ኃያል ሊያደርጋት እንደሚችልም ተጠቁሟል።
አልጀዚራ እንደዘገበው አሜሪካ እና ቻይና በበረታ የቴክኖሎጂ ፉክክር ውስጥ ገብተዋለ።

ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top