በተያዘው ዓመት ከ75 ሺህ ቶን በላይ የአበባ ምርት ወደተለያዩ የአውሮፓ አገራት ተልኳል- የኢትዮጵያ አየር መንገድ

1 Yr Ago
በተያዘው ዓመት ከ75 ሺህ ቶን በላይ የአበባ ምርት ወደተለያዩ የአውሮፓ አገራት ተልኳል- የኢትዮጵያ አየር መንገድ
በተያዘው ዓመት ከ75 ሺህ ቶን በላይ የአበባ ምርት ወደተለያዩ የአውሮፓ አገራት መላኩን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ገልፀዋል።
ይህ የተገለጸው በ8ኛው ሆርቲፍሎራ የአበባ ምርቶች ኤግዚቢሽን እና ባዛር ላይ ነው።
የሎጂስቲክስ ስራውን ለማሳለጥ ሰፋፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል።
ባዛሩ ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ 3 ቀናት በሚሊኒየም አዳራሽ የሚካሄድ ሲሆን በአውደርዕዩ ላይ የአበባ አምራቾች፣ ኢንቨስተሮች፣ ኤክስፖርተሮች እና ባለድርሻዎች ተገኝተዋል።
እየተካሄደ በሚገኘው የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይም የግብርና ሚኒስትር ዶ/ር ግርማ አመንቴ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰውን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
የአበባ ምርት 2ኛው የኤክስፖርት የገቢ ምንጭ ሲሆን ኢትዮጵያ ከዘርፉ የምታገኘውን ገቢ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የሆርቲካርቸል አሶሴሽን የቦርድ ሰብሳቢ ነጋ መኳንንት በመክፈቻው ላይ ተናግረዋል።
የግብርና ሚኒስትሩ ዶ/ር ግርማ አመንቴ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ከዘርፉ የምታገኘውን ገቢ ለማሳደግ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
በፈረንጆቹ ከ2004 እስከ 2022 ባሉት አመታት ከአበባ ምርት 4 ቢሊየን ዶላር ገቢ የተገኘ ሲሆን ከ200 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር እንደተቻለ በመድረኩ ተነስቷል።
በአሚር ጌቱ

ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top