ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ወንጀሎችን በመከላከል እያበረከተች ለሚገኘው ድርሻ እውቅና ተሰጣት

1 Yr Ago
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ወንጀሎችን በመከላከል እያበረከተች ለሚገኘው ድርሻ እውቅና ተሰጣት
‘ሮክ’ የተሰኘው በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ የሚሰራው ድርጅት ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ሲያካሂድ በቆየው ጉባኤ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ወንጀሎችን በመከላከል እያበረከተች ለሚገኘው ድርሻ እውቅና ሰጥቷታል።
በድንበር ዘለል ወንጀሎች ዙሪያ የሚሰራው ROCK የተባለው ድርጅት ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ሲያካሂድ የቆየውን ጉባኤውን በዛሬው ዕለት አጠናቋል።
ኢትዮጵያን ጨምሮ ግብፅ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ጂቡቲ ፣ኤርትራ፣ ኬንያ፣ ሊቢያ፣ ቱኒዚያ፣ ዩጋንዳ እና ሶማሊያ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ በመመላከል ተጨባጭ ለውጥ ማምጣታቸው ተገልጿል።
በሮክ አማካኝነት ከ700 በላይ የወንጀል መረጃዎችን በመሰብሰብ አባል ሀገራት በጋራ እንዲከላከሉ ለማስቻል መረጃ ለኢንተርፖል ማድረሳቸው ተገልጿል።
የምስራቅ እፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ትብብር ድርጅት ዋና ስራአስፈፃሚና የኢንተርፖል ቀጣናዊ ቢሮ ሊቀመንበር ጌዴዮን ከሚሊ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች ሀገራት ለሮክ ፕሮጀክት መሳካት የነቃ ትሳትፎ እያደረጉ መሆኑን እንስተዋል።
ኢትዮጵያ በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በኢንተርፖል የሚፈለጉ ወንጀሎችን ጭምር አጋልጦ በመስጠት በቀጣናው ያለውን ህገወጥ እንቅስቃሴ ለመግታት የሚደረገውን ጥረት እያገዘች መሆኑንም ጠቅሰዋል ሊቀመንበሩ።
የሜዲተራኒያን አካባቢ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ብሎም ሌሎች ዓለም አቀፍ ወንጀሎች የሚፈፀምበት ቀጣና ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ ከሊቢያን ደቡብ አፍሪካ ሸሽተው የሚመጡ ወንጀለኞችን አሳልፋ መስጠቷ ያስመሰግናታል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርምራ ቢሮ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል ዘላለም መንግስቴ ፣ በአውሮፖና በሌሎች ሀገራት በኢንተርፖል የመያዣ ትእዛዝ የወጣባቸው ህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን አሳልፈን ሰጥተናል ብለዋል።
እንዲህ አይነቱ የትብብር ስራ ተጠናክሮ እንዲቀል ሮክ ቢሮውን አዲስ አበባ እንዲከፍት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ መጠየቁን ምክትል ኮሚሽነር ጀነራሉ አስታውሰዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top