በኢትዮጵያ የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተጨባጭ ለውጦች የመጡበት ነው፦ አንቶኒ ብሊንከን

1 Yr Ago
በኢትዮጵያ የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተጨባጭ ለውጦች የመጡበት ነው፦ አንቶኒ ብሊንከን
በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት በኢትዮጵያ የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተጨባጭ ለውጦች የመጡበት መሆኑን የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ተናገሩ።
በኢትዮጵያ ለውጥ እንዲመጣ ቁርጠኝነት ላሳዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
በአንድ በኩል ግጭት መቆሙ በሌላ በኩል ደግሞ በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች የሚደረገው የሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉ እና የአገልግሎቶች ዳግም መጀመር አበረታች ለውጥ ነው ብለውታል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጦርነቱን ተከትሎ በኢትዮጵያ የደረሰውን የምጣኔ ሀብት ጫና ለማቅለል አሜሪካ በአጋርነት እንደምትሠራም አረጋግጠዋል።
አሜሪካ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል ከ331 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ እንደምታደርግም ገልጸዋል።
በምሥክር ስናፍቅ

ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top