የሃማስ መሪ እስማኤል ሃኒዬ በቴህራን መገደላቸው ተነገረ

1 Mon Ago 426
የሃማስ መሪ እስማኤል ሃኒዬ በቴህራን መገደላቸው ተነገረ

የሃማስ መሪው እስማኤል ሃኒዬ በቴህራን በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው እስራኤል ባደረሰችው ጥቃት መገደላቸው ቢቢሲ ዘግቧል።

በጉዳዩ ላይ እስራኤል እስካሁን ያለችው ነገር ባይኖርም ጥቅምት 7 ለደረሰባት ጥቃት እና 1,200 እስራኤላውያንን መገደላቸውን ተከትሎ የሃማስ መሪዎችን አጠፋለሁ ማለቷ ይታወሳል ብሏል በዘገባው።

እስራኤል በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት በፈጸመችው ጥቃት የሂዝቦላህ ከፍተኛ አዛዥን መግደሏን በተናገረች በሰዓታት ልዩነት ውስጥ ነው የሃኒዬ ሞት ይፋ የተደረገው።

በኢራን እንደሚደገፉ የሚነገርላቸው የሁለት ቡድን መሪዎች በ24 ሰአታት ውስጥ በተፈፀመው ጥቃት መገደላቸውን ተከትሎ ቀጠናው በቅርቡ ወደ ሌላ ግጭት ሊገባ ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል።

እስማኤል ሃኒዬ ለበርካታ አመታት ኑሯቸውን በኳታር ያደርጉ ሲሆን አዲስ የተመረጡት የኢራኑን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን በዓለ ሲመት ላይ ለመታደም ነው ቴህራን የተገኙት ተብሏል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top