ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻ ለኢትዮጵውያን ለሽያጭ መቅረቡን አበሰሩ

1 Mon Ago 568
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻ ለኢትዮጵውያን ለሽያጭ መቅረቡን አበሰሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻ ለኢትዮጵውያን ለሽያጭ መቅረቡን በዛሬው ዕለት አብስረዋል። 

ኢትዮ ቴሌኮም ትርፋማ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ስቶክ ማርኬትን ለማለማመድ የኩባንያው 10 በመቶ ለሽያጭ መቅረቡን ገልፀዋል። 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ኢትዮጵያውያን ለሽያጭ የቀረቡትን የኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮኖች በሽሚያ እንዲገዙ ጥሪ አቅርበዋል። 

ስቶክ ማርኬት በይበልጥ በጥቅም ላይ መዋል ስላለበት ኢትዮጵያውያን ዕድሉን ሊጠቀሙበት ይገባል ነው ያሉት። 

ኢትዮ ቴሌኮም አጠቃላይ ያለው 100 ቢሊዮን የተከፈለ የገበያ ድርሻ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ 10 በመቶው ነው በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለሽያጭ ይፋ የተደረገው።

ይህን 10 በመቶ ድርሻ ኢትዮጵያውያን ከዛሬ ጀምሮ እስከ ታህሣስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በቴሌብር አማካይነት መግዛት እንደሚችሉ ተገልጿል። 

የእያንዳንዱ አክሲዮን ዋጋ 300 ብር መሆኑ እና እያንዳንዱ ሰው ከ33 እስከ 3 ሺህ 333 አክሲዮኖች መግዛት እንደሚችልም ታውቋል።

ኢትዮ ቴሌኮም ወደ አክሲዮን ማህበርነት መቀየሩንም የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ አስታውቀዋል። 

በተመስገን ሽፈራው


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top