ሳዑዲ ዓረቢያ የ2034ቱን የዓለም ዋንጫ አዘጋጅ ሆና ተመረጠች

1 Mon Ago 228
ሳዑዲ ዓረቢያ የ2034ቱን የዓለም ዋንጫ አዘጋጅ ሆና ተመረጠች

ሳዑዲ ዓረቢያ የ2034ቱን የዓለም ዋንጫ አዘጋጅ ሆና መመረጧን ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) አስታውቋል፡፡

ፊፋ ዛሬ ባካሄደው ልዩ ጉባኤ የ2030 የዓለም ዋንጫን ሞሮኮ፣ ስፔን እና ፖርቹጋል በጋራ እንዲያዘጋጁ መመረጣቸውንም ገልጿል፡፡

የዓለም ዋንጫን 100ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ 3 ጨዋታዎች በአርጀንቲና፣ በኡራጓይ እና ፓራጓይ እንደሚደረጉ ተጠቁሟል፡፡

የሁለቱም የአለም ዋንጫዎች አስተናጋጆች ዛሬ በተደረገው የፊፋ ልዩ ጉባኤ በድምጽ ብልጫ መረጋገጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top