ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቦሌ ካርጎ እስከ አቃቂ ድልድይ በመሰራት ላይ የሚገኘውን የአረንጓዴ ልማት ስራ ጎበኙ

1 ወር በፊት
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቦሌ ካርጎ እስከ አቃቂ ድልድይ በመሰራት ላይ የሚገኘውን የአረንጓዴ ልማት ስራ ጎበኙ

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቦሌ ካርጎ እስከ አቃቂ ድልድይ በመሰራት ላይ የሚገኘውን የአረንጓዴ ልማት ስራ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ከንቲባዋ ከጉብኝቱ በኋላ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ፤ ከተማዋን ጽዱ፣ ውብ እና አረንጓዴ ለማድረግ የተጀመረው የኮሪደር ልማት አካል የሆነው ይህ የአረንጓዴ ልማት ስራ የህጻናት መጫዎቻዎችን፣ መናፈሻዎችን እንዲሁም የተለያዩ ለአካባቢው ነዋሪዎች ግልጋሎት የሚሰጡ ስራዎችን ያካተተ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የአረንጓዴ ልማት ስራው ከ200 ሺሕ ካሬ በላይ ሽፋን ያለው እና ከቦሌ ካርጎ እስከ አቃቂ ድልድይ ድረስ 9.5 ኪሎ ሜትር የሚረዝም መሆኑን የጠቀሱት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ስራውን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለህዝብ ክፍት እንደሚደረግም ጠቅሰዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top