ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት እያበረከተች ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው - የዩኤንሶም ኃላፊ ካትሪዮና ላይንግ

19 ቀን በፊት
ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት እያበረከተች ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው - የዩኤንሶም ኃላፊ ካትሪዮና ላይንግ

ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት እያበረከተች ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን  የተመድ ዋና ፀሐፊ የሶማሊያ ተወካይ እና በተባበሩት መንግስታት የሶማሊያ የድጋፍ ተልዕኮ (ዩኤንሶም) ኃላፊ ካትሪዮና ላይንግ ገለፁ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከተመድ ዋና ፀሐፊ የሶማሊያ ተወካይ እና በተባበሩት መንግስታት የሶማሊያ የድጋፍ ተልዕኮ (ዩኤንሶም) ኃላፊ ካትሪዮና ላይንግ ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።

በውይይታቸውም፤ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በኢትዮጵያ እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መካከል ያለውን አጋርነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ በውይይቱ ወቅት፤ ኢትዮጵያ በቀጠናው ሰላምና መረጋጋትን ለማስቀጠል ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

የዩኤንሶም ኃላፊ ካትሪዮና ላይንግ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት እያበረከተች ያለው ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚደነቅ መሆኑን መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top