በተገባደደው አውሮፓውያኑ 2022 ዓ.ም በዓለም አቀፍ ደረጃ 100 ሚሊዮን ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን ተመድ ገለፀ

1 Yr Ago 898
በተገባደደው አውሮፓውያኑ  2022 ዓ.ም በዓለም አቀፍ ደረጃ 100 ሚሊዮን ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን ተመድ ገለፀ

በተገባደደው አውሮፓውያኑ  2022 ዓ.ም በዓለም አቀፍ ደረጃ 100 ሚሊዮን ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን(UNHCR) አስታወቀ፡፡

እንደ ድርጅቱ ዘገባ በ2021 ከነበረው 90 ሚሊዮን ተፈናቃዮች ቁጥር በ2022 በ10 ሚሊዮን አሻቅቧል ያለው ድርጅቱ እነዚህ በችግር ላይ ያሉ ተፈናቃዮችን ለመርዳት ጥረት እያደረገ  መሆኑን አስታውቋል፡፡

የከሞሽኑ ኃላፊ ፊሊፒኖ ግራንዲ እንዳሉት እስካሁን ይህን ያህል የተፈናቃይ ቁጥር ከዚህ ቀደም ተመዝግቦ  አያውቅም ብለዋል።

በዋናነት   እዚህም እዚያም የሚፈነዱ ስርዓት አልበኝነትና ነውጠኝነት እንዲሁም  ረዘም ላላ ጊዜ የወሰዱ ግጭቶች የመፈነቃሉ ምክንያቶች እንደነበሩ የገለፀው ድርጅቱ ፤ ዩክሬን፣ ኢትዮጵያ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ሶሪያ እና ማይናማር  ያሉ አገራት አብዛኛው ህዝብ የተፈናቀለባቸው ሀገራት መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡

በአየር ንብረት መዘባት ምክንያት እየተከሰቱ ያሉ የተፈጠሮ አደጋዎች እና ድርቅ ከግጭት ቀጥሎ ለብዙ ህዝብ መፈናቀል መንስኤ መሆኑም ተመልክቷል።

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ልማትን ፣ ሰላም ግንባታን፣ ሰብአዊ መብት ጥበቃን በማቀናጀት እና የአየር ንብረት ለውጥ እና የተፈጥሮ አደጋዎችን በመከላከል ረገድ  ርበርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግ  የተ.መ.ድ ዋና ፀሓፊ አንቶንዮ ጉታሬዝ በ2022 ዓ.ም በስደተኞ ዙሪያ በተጀመረው አዲስ አጀንዳ  ላይ ማሳሰበቸው የቻይና  ደይሊ ዘገባ  አስታውሷል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top