በ44ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አውስትራሊያ ባትረስት ከተማ ሰሞኑን በተካሄደው ውድድር ላይ በ2 ወርቅ፣ በ7 ብር፣ በ1 ነሃስ በድምሩ በ10 ሜዳልያዎች ከአለም ሃገራት 2ኛ ደረጃን የያዘው የኢትዮጵያ ስፖርት ልኡካን ቡድን ወደ ሀገሩ ተመልሷል፡፡
የስፖርት ልኡካኑ አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና ሌሎች አመራሮች አቀባበል አድርገውለታል።
ለአትሌቶቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላፉት አምባሳደር መስፍን የቡድኑ አባላት ላስመዘገቡት ድል ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ለስፖርት ልኡካን ቡድኑ ዛሬ ከረፋዱ 4:00 ላይ በስካይ ላይት ሆቴል የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ፕሮግራም እንደሚካሄድ ከኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡