በሙስና ተግባር በተጠረጠሩ 640 ሰዎች ላይ ክስ ተመሥርቷል፦ ብሔራዊ የፀረ ሙስና አስተባባሪ ኮሚቴ

1 Yr Ago
በሙስና ተግባር በተጠረጠሩ 640 ሰዎች ላይ ክስ ተመሥርቷል፦ ብሔራዊ የፀረ ሙስና አስተባባሪ ኮሚቴ
በሙስና ተግባር በተጠረጠሩ 640 ሰዎች ላይ ክስ መመሥረቱን ብሔራዊ የፀረ ሙስና አስተባባሪ ኮሚቴ አስታወቀ።
የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ተመስገን ጥሩነህ እንዳሉት፣ ባለፉት ወራት 759 ጥቆማዎች ለብሔራዊ ኮሚቴው ቀርበዋል።
ከዚህም ውስጥ በ175ቱ ላይ ምርመራ መደረጉን እና 81ዱ ምርመራቸው ተጠናቆ የክስ መዝገባቸው መደራጀቱን ገልጸዋል።
በዚህም በሙስና ተግባር በተጠረጠሩ 640 ሰዎች ላይ ክስ መመሥረቱን ተናግረዋል።
አቶ ተመስገን ጥቆማዎችን መሠረት አድርጎ በተደረገው የማጣራት ሥራ ከ2.2 ቢሊዮን ብር በላይ በመንግሥት እና ሕዝብ ሀብት ላይ ጉዳት መድረሱ ተረጋግጧል ብለዋል።
የሙስና ተግባር የሚፈፀምበትን መረብ መበጠስ ካልተቻለ በሀገር እና ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርስ ገልጸው፣ በተግባሩ የሚሳተፉ አካላትን ማጋለጥ እና አሳልፎ መስጠት ከኅብረተሰቡ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል።
የብሔራዊ እና የክልል ፀረ ሙስና ኮሚቴ ሰብሳቢዎች እና አባላት ግምገማ እየተካሄደ ይገኛል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top