ለሁለት ሚሊዮን ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል - የስራና ክህሎት ሚኒስቴር

1 Yr Ago
ለሁለት ሚሊዮን ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል - የስራና ክህሎት ሚኒስቴር
ባለፉት ስምንት ወራት ለሁለት ሚሊዮን ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን የስራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ይህም የዕቅዱ 77 በመቶ መሆኑን በደብረ ብርሃን እየተገመገመ ባለው የበጀት ዓመቱ የሰባት ወራት የእቅድ ክንውን ግምገማ ላይ የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታው ንጉሱ ጥላሁን ያስታወቁት።
ከተፈጠረው የሥራ ዕድል ውስጥ ግብርናው የ39.2 በመቶ፣ ኢንዱስትሪው የ19.7 በመቶ እና የአገልግሎት ዘርፉ ደግሞ የ41.1 በመቶ ድርሻ አለው።
በኢትዮጵያ እየተፈጠሩ ያሉ ስራዎች ከኢንዱስትሪዎች ይልቅ የአገልግሎት ዘርፉ ማደጉ እንዳሳሰባቸውም ጠቁመዋል።
በመሆኑም፣ በተለያየ አካባቢ የሚገኙ የስራ ኃላፊዎች ኢንዱስትሪዎችን ለማስፋፋት የተቀላጠፈ አገልግሎት እና የመስሪያ ቦታ እንዲያቀርቡም ጠይቀዋል።
የሰለጠኑ ዜጎች በውጪ ሀገራት የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ባለፉት ወራት እየተሰራ መሆኑን እና ወደ አራት የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ለመላክ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገልጿል።
ብርሃን እያየሁ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top