ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የማራቶን ውድድሮች ድል አስመዝግበዋል

1 Yr Ago
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የማራቶን ውድድሮች ድል አስመዝግበዋል

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የማራቶን ውድድሮች ድል ማስመዝገብ ችለዋል።

በቻይና ሸንዤን በተደረገ ማራቶን በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያኑ ድል የቀናቸው ሲሆን፤በወንዶች አትሌት ባንታየሁ አዳነ በሴቶች አገሬ ታምር በአንደኝነት አጠናቀዋል።

በአሜሪካ ሎሳንጀለስ በተካሄደ የወንዶች ማራቶን አትሌት ጀማል ይመር ቀዳሚ መሆን ሲችል ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት የማነ ጸጋዬ ደግሞ ሁለተኛ ሆኖ ውድድሩን ጨርሷል።

በባርሴሎና በተደረገ የማራቶን ውድድርም ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ዘይነባ ይመር ውድድሩን በአንደኝነት ስታጠናቅቅ በአሜሪካ የኒዮርክ ግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ ደግሞ በሴቶች አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ ሁለተኛ ሆና ውድድሯን ጨርሳለች።

በታይዋን ርዕሰ ከተማ ታይፔ በተደረገው የሴቶች ማራቶን ውድድርም እንዲሁ ኢትዮጵያውያኑ በቀለች ጉደታ፣ መሰረት ድንቄ እና ገበያነሽ አየለ ከአንድኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ አሸንፈዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top