ሎሬት ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

1 Yr Ago
ሎሬት ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
በብዝሃ ሕይወት ሳይንቲስትነት አንቱታን ያተረፉት ሎሬት ዶ/ር ተወልደብርሃን ገብረእግዚአብሔር ባደረባቸው ሕመም በ83 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
 
የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪ እና ተከራካሪ የነበሩት ዶ/ር ተወልደብርሃን ገብረእግዚአብሔር ከአባታቸው ከቄስ ገብረእግዚአብሔር ዮሐንስ እና ከእናታቸው ወ/ሮ መዓዛ ወልደ መድኅን በትግራይ ክልል ዐድዋ ርባገረድ መንደር የካቲት 12 ቀን 1932 ዓ.ም ተወለዱ።
 
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በንግሥተ ሳባ 1ኛ ደረጃ እንዲሁም ወደ ጀኔራል ዊንጌት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በማምራት በ1959 ዓ.ም በከፍተኛ ውጤት ወደ ቀድሞው ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገብተዋል።
 
ሎሬት ዶ/ር ተወልደብርሃን በሕይወት ዘመናቸው ለአገራቸው ያበረከቱት አስተዋጽኦ እና አርዓያነታቸው በጉልህ ቀለም ከሚጻፍላቸው ጀግና ኢትዮጵያዊያን መካከል በግንባር ቀደምትነት የተቀመጡ ነበሩ።
 
በብዝሃ ሕይወት ጥናት እና ምርምርም በርካታ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን ማግኘት ችለዋል።
 
ዶ/ር ተወልደ ብርሃን የሦስት ሴቶች ልጆች አባት ሲሆኑ ከ60 በላይ ሌሎች ልጆችን ያሳደጉ ልበ ቀና ሰው ነበሩ።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top