በሾላ ገበያ በደረሰ የእሳት አደጋ 50 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወደመ

1 Yr Ago
በሾላ ገበያ በደረሰ የእሳት አደጋ 50 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወደመ
 
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ሾላ ገበያ በደረሰ የእሳት አደጋ 50 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
ትናንት ሌሊት 10 ሰዓት አካባቢ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በሾላ ገበያ ማዕከል ከሚገኙ 1 ሺህ 600 ሱቆች ውስጥ 84 የሚሆኑት ላይ የእሳት አደጋ መድረሱን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ገልጸዋል።
የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ባደረጉት ርብርብ ወደ ሌሎች ተዛምቶ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ አደጋውን መቆጣጠር መቻሉን ጠቁመው፣ ከ1 ሺህ 516 የሚሆኑ የንግድ ሱቆችን ማትረፍ ተችሏል ብለዋል።
በዚህም 500 ሚለየን ብር የሚገመት ንብረት ከአደጋው ማትረፍ መቻሉን ጠቁመዋል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።
በአደጋው እስካሁን በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ጠቁመው፣ የአደጋ መንስኤም እየተጣራ መሆኑን ተናግረዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top