ጤናን የሚጎዱ ምግብ እና መድኃኒት በማምረት እና በማከፋፈል ላይ የነበሩ ከ500 በላይ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ

1 Yr Ago
ጤናን የሚጎዱ ምግብ እና መድኃኒት በማምረት እና በማከፋፈል ላይ የነበሩ ከ500 በላይ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ
የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ባለሥልጣን የኅብረተሰቡን ጤና የሚጎዱ ምግብ እና መድኃኒትን በማምረት እና በማከፋፈል ላይ የነበሩ ከ500 በላይ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገለጸ። እርምጃ ከተወሰደባቸው ድርጅቶች 388 በምግብ ዘርፍ የተሰማሩ ሲሆኑ ከ120 የማያንሱት ደግሞ በመድኃኒት ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች መሆናቸው ታውቋል። ምግብን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው ለኅብረተሰቡ ሲያሰራጩ የነበሩ አራት ግለሰቦችም የእስራት እና የገንዘብ ቅጣት እንደተወሰነባቸው ኢዜአ ዘግቧል። በ2014 በጀት ዓመት ለ4 ሺህ 510 አዲስ የምግብ ዓይነቶችን በመመዝገብ የገበያ ፈቃድ መሰጠቱን የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሔራን ገርባ ገልጸዋል።
ከዚህም ባሻገር ከ3.6 ሚሊየን ቶን በላይ ምግብ ተገቢው ፍተሻ ተደርጎ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ ፈቃድ መስጠቱን ገልጸዋል።
 
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ 
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top