የሠራዊቱን ግዳጅ የመፈጸም አቅም በማጎልበት የሀገርን ሰላም የማስከበር ሥራው ይጠናከራል ፡- ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ

8 Mons Ago
የሠራዊቱን ግዳጅ የመፈጸም አቅም በማጎልበት የሀገርን ሰላም የማስከበር ሥራው ይጠናከራል ፡- ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ

የሀገር መከላከያ ሠራዊት ግዳጅ የመፈጸም አቅምን በማጎልበት የሕዝብን ሰላምና ደህነት ለማረጋገጥ የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ ገለጹ።

ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ የመከላከያ ሠራዊቱን ግዳጅ የመፈጸም ብቃቱን ማጎልበት የዘወትር ተግባር ሆኖ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል፡፡

ሠራዊቱ ግዳጅ የመፈጸም አቅሙን በማጎልበት የሕዝቡን ብሎም የሀገርን ሰላም በዘላቂነት ለማጽናት የጀመራቸውን ሥራዎች አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።

የመከላከያ ሠራዊቱ በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጣናዎች ሁሉ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃትና በድል አድራጊነት እየተሻገረ የሕዝቡን ሰላም እያረጋገጠ መሆኑን አመልክተዋል።

በቄለም ወለጋ የሸኔ የሽብር ቡድን ሲፈጥር የነበረውን የጸጥታ ችግር ለማስቆም ሠራዊቱ ባካሄደው ሕግ የማስከበር ዘመቻ በአካባቢው ሰላም መስፈኑን ተናግረዋል።

በቀጣይም ሠራዊቱ ከህዝቡ ጋር ተቀናጅቶ የተገኘውን ሰላም ለማጽናት እና ለማረጋገጥ ከሰላም ወዳዱ ህዝብ ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን ሌተናል ጄኔራሉ ገልጸዋል።

የቄለም ወለጋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መንግስቱ ደረሱ በበኩላቸው፤ የዞኑ ሕዝብ ባለፉት አራት ዓመታት የሸኔ የሽብር ቡድን በፈጠረው የጸጥታ ችግር ህዝቡ በሰላም እጦት ሲሰቃይ መቆየቱን አስታውሰዋል።

ይሁን እንጂ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ባካሄደው ሕግ የማስከበር ዘመቻ በአካባቢው ሰላም መስፈኑን መናገራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

በዞኑ የተገኘውን ሰላም ይበልጥ ለማጠናከር የዞኑ ህዝብና አስተዳደር ከሠራዊቱ ጎን በመሆን እየሰራ መሆኑን ምክትል አስተዳዳሪው አስታውቀዋል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top