ሀሪ ኬን የመጀመሪያ ዋንጫውን አሳካ

8 Hrs Ago 45
ሀሪ ኬን የመጀመሪያ ዋንጫውን አሳካ
እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጫዎች ሀሪኬን በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በባየርን ሙኒክ ቤት ዋንጫ ማሳካት ችሏል።
 
በዛሬው የቦንደስሊጋ መርሀ ግብር ባየርሊቨርኩሰን ከፍራይበርግ 2 አቻ መለያየቱን ተከትሎ ባየርሙኒክ ለ34ኛ ጊዜ የቦንደስሊጋ ሻምፒዩን መሆኑን አረጋግጧል።
 
ከባየርሙኒክ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘው ባየር ሊቨርኩሰን ከእንግዲህ ያሉትን 2 ጨዋታዎችን እንኳን ቢያሸንፍ እና ባየርሙኒክ ሁለቱንም ቢሸነፍ በመካከላቸው የ2 ነጥብ ልዩነት እያለ ባየርሙኒክ ያሸነፋል።
 
በመሆኑም ባየርሙኒክ 2 ጨዋታዎች እየቀሩት የ 2024/25 የቦንደስሊጋ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል።
 
ታዲያ ሀሪ ኬንም ከ16 አመታት ጥበቃ በኋላ ህልሙን አሳክቷል። እግር ኳስም በስተመጨረሻ ያከበራትን አክብራለች።
 
በሴራን ታደሰ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top