ደቡብ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ትብብሮች ላይ 'ሥር ነቀል' ለውጥ እንዲደረግ ጠየቀች

8 Mons Ago
ደቡብ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ትብብሮች ላይ 'ሥር ነቀል' ለውጥ እንዲደረግ ጠየቀች

አዲሱ የደቡብ የዓለም ሥርዓት ፍላጎት እየበረታ መሆኑን የደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ሚንስትር ናሌዲ ፓዶር ገልጸዋል።

አፍሪካ ግን ከታላላቅ የኢኮኖሚ ኃይሎች ትብብሮች ሙሉ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እስካሁን እንዳላገኘችም ሚኒስትሯ መናገራቸውን የአርቲ ዘገባ ያመለክታል።

ናሌዲ ፓዶር ይህን ያሉት የተለያዩ ሀገራት ልዑካን ከዓለም አቀፉ አስተዳደር ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት በደቡብ አፍሪካዋ ኬፕ ታውን የተሰበሰቡበት ፎረም መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

ሚኒስትሯ "እነዚህ የትብብር ድርጅቶች ያላከናወኑት ነገር ብዙ ነው፤ በአፍሪካ ውስጥ የኢንዱስትሪ አቅም እንዲጨምር፣ የኃይል አቅርቦት እንዲሰፋ፣ ስማርት ማኑፋክቸሪንግ እንዲያድግ አላደረጉም" ብለዋል።

ናሌዲ ፓንዶር እንዳሉት "አሁን ያሉት ኅብረቶች እነዚህን ነገሮች በትክክል ማመንጨት አለባቸው፤ አፍሪካን ነፃ የሚያደርጋት ይህ ነው፤ እነዚህ ነገሮች ባይኖሩ የእኛ አጋርነት የምልጃ አጋርነት እንጂ የእውነተኛ ልማት አጋርነት አይደለም" ብለዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top