አስገራሚ እውነታዎች፦ ስለኢንተርኔት

7 Mons Ago
አስገራሚ እውነታዎች፦ ስለኢንተርኔት
 • በኢንተርኔት (በበይነመረብ) ፈጣሪነት ዋና ተጠቃሾች አሜሪካውያኑ ኮምፒዩተር ሳይንቲስቶች ቪንተን ሰርፍ እና ሮበርት ካን ናቸው።
 • ሳይንቲስቶቹ መረጃ በተለያዩ አውታረ መረቦች መካከል እንዴት እንደሚጋራ የሚገልጽ ስታንዳርድ ወይም የማስተላለፊያ ቁጥጥር ፕሮቶኮል እና የበይነመረብ ፕሮቶኮል /Transmission Control Protocol and Internet Protocol (TCP/IP)/ የሚባለውን ያወጡ ናቸው።
 • የዓለማችን የመጀመሪያው ድረ ገጽ ‘ወርልድ ዋይድ ዌብ’ (www) ነው። ይህን የኮምፒዩተር የድረ ገጽ ሥርዓት የፈጠረው እንግሊዛዊው ሳይንቲስት ሰር ቲሞቲ በርነርስ ሊ ነው። ጊዜውም እ.አ.አ በ1989 ነበር።
 • የዓለማችን የመጀመሪያው ሕጋዊ ምዝገባ የፈጸመ ድረ ገጽ symbolics.com ነው።
 • ወደ 2 ቢሊዮን የሚጠጉ (ከ1.98 ቢሊዮን በላይ) ድረ ገጾች ኦንላይን ይገኛሉ። ከእነዚህ ውስጥ በቋሚነት አገልግሎት የሚሰጡት ከ300 ሚሊዮን የማይበልጡት ናቸው።
 • በተገልጋይ ብዛት ቁጥር አንዱ የዓለማችን ድረ ገጽ ጉግል ነው። ዩቲዩብ እና ፌስ ቡክ ደግሞ ተከታዮቹን ደረጃዎች ይይዛሉ።
 • ዓለም ላይ 5.47 ቢሊዮን የኢንተርኔት ተጠቃሚ ሕዝብ አለ። ከ25 ዓመታት በፊት የዓለም የኢንተርኔት ሽፋን 1 በመቶ ብቻ ነበር።
 • የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ዓመታዊ ዕድገት ምጣኔ በአማካይ 8.2 በመቶ ነው።
 • 4.32 ቢሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ኢንተርኔትን የሚጠቀሙት በሞባይል ስልኮቻቸው ነው።
 • በዓለም ላይ 32 በመቶ የሚሆኑ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ዕድሜአቸው ከ25 እስከ 34 ዓመት መካከል ያሉ ሰዎች ናቸው።
 • ገመድ አልባ ኢንተርኔት (ዋይ ፋይ) የተፈጠረው በ1990 ዓ.ም ነው።
 • ኢንተርኔት ማግኝት ሕጋዊ የዜጎች መብት ያደረገች የመጀመሪያዋ ሀገር ፊንላንድ ናት። ጊዜውም እ.አ.አ በ2010 ዓ.ም ነበር።
 • እ.አ.አ ጥቅምት 2023 በዓለም ላይ 5.3 ቢሊዮን ንቁ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች አሉ፤ ይህም ማለት ከአጠቃላይ የዓለም ሕዝብ 65.7 በመቶ የሚሆነው ነው።
 • ከ5.3 ቢሊዮን ንቁ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች መካከል ደግሞ 4.95 ቢሊዮም (61.4) በመቶ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ናቸው።
 • አብዛኛው ሰዓታቸውን ኢንተርኔት በመጠቀም የሚያሳልፉ ሰዎች ለብቸኝነት፣ ለድብርት እና ለአዕምሮ አለመረጋጋት የተጋለጡ ናቸው።
 • ኢንተርኔት ከልክ በላይ የመጠቀም (ሱሰኛ የመሆን) የሥነ-አዕምሮ ሕመም፣ ኢንተርኔት አዲክሽን ዲስ-ኦርደር (Internet Addiction Disorder /IAD) ተብሎ ይጠራል።
 • የሳይበር ወንጀል በ2023 በዓለም አቀፍ ደረጃ 8 ትሪሊዮን የአሜሪካ ዶላር ኪሳራ ሊያስከትል እንደሚችል ሳይበር ሴኩሪቲ ቬንቸርስ ያስቀመጠው ትንበያ ይጠቁማል።
 • ይህም በወር 667 ቢሊዮን፣ በሳምንት 154 ቢሊዮን፣ በቀን 21.9 ቢሊዮን፣ በሰዓት 913 ሚሊዮን፣ በደቂቃ 15.2 ሚሊዮን እንዲሁም በሰከንድ 255 ሺህ ዶላር ኪሳራ መሆኑ ነው።
 • በቀን ከ6 ቢሊዮን በላይ ጥያቄዎች ጉግል ላይ ይፈለጋሉ።
 • በዓለማችን በየቀኑ ከ500 ሚሊዮን በላይ የትዊተር መልዕክቶች ይለቀቃሉ።
 • ዩቲዩብ ላይ በየአንድ ደቂቃው ርዝማኔያቸው 500 ሰዓት የሚደርስ ቪዲዮዎች ይጫናሉ።
 • የመጀመሪያው ትዊተር ላይ የተጻፈው መልዕክት “Just setting up my twttr” የሚል ነበር። መልዕክቱን የጻፈውም የትዊተር መሥራች የሆነው ጃክ ፓትሪክ ዶርሲ ሲሆን ጊዜውም እ.አ.አ መጋቢት 21 ቀን 2006 ነበር።

በኢዮብ መንግሥቱ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top