አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ከአሜሪካ የልማት ተራድኦ ድርጅት ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

7 Mons Ago
አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ከአሜሪካ የልማት ተራድኦ ድርጅት ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ከአሜሪካ የልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩ.ኤስ.አይ.ዲ) ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ስኮት ሆክላንደር ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም፤ በክልሉ የምግብ እርዳታ አቅርቦትን ዳግም ማስጀመር እና ድጋፉን ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ማድረስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የአሜሪካ የልማት ተራድኦ ድርጅት የስራ ሀላፊዎች መገኘታቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top