ኢትዮጵያ በአረንጎዴ አሻራ እየሰራች ያለው ስራ ለአፍሪካ ምሳሌ የሚሆን ነው፡- አቡበከር ክያሪ

9 Mons Ago 191
ኢትዮጵያ በአረንጎዴ አሻራ እየሰራች ያለው ስራ ለአፍሪካ ምሳሌ የሚሆን ነው፡- አቡበከር ክያሪ
ኢትዮጵያ በአረንጎዴ አሻራ እየሰራች ያለው ስራ ለአፍሪካ ምሳሌ መሆን እንደሚችል የናይጀሪያ የግብርና እና የምግብ ዋስትና ሚኒስትር አቡበከር ክያሪ ገለጹ፡፡
 
ኢትዮጵያ በተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ዱባይ እየተካሄደ ባለው ኮፕ 28 የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ አረንጓዴ አሻራ መካነ ርዕይ (ፓቪሊዮን) ለይታ አቅርባለች።
 
የናይጄሪያ የግብርና እና የምግብ ዋስትና ሚኒስትር አቡበከር ክያሪ ኮፕ 28 የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ አረንጓዴ አሻራ መካነ ርዕይ (ፓቪሊዮን) ጎብኝተዋል።
 
ሚኒስትሩ በጉብኝታቸውም ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ እያከናወነችው ያለው ተግባራት የሚያስደንቅ ነው ብለዋል፡፡
 
በኢትየጵያ እየተከናወነ ያለው የአረንጎዴ አሻራ ለናይጄሪያ ብሎም ለመላው አፍሪካ ምሳሌ መሆን ይችላልም ሲሉ ተናግረዋል።
 
ናይጄሪያ የአረንጓዴ ልማት ላይ ተመሳሳይ ተግባራት እያከናወነች መሆኑን የጠቆሙት ሚነስትሩ፤ ኢትየጵያ በአረንጓዴ አሻራ ያገኘችውን ይህን መሰል ውጤት ናይጄሪያ ልምድ መውሰድ ትፈልጋለች ብለዋል።
 
በመሆኑም ለዚህ የአረንጎዴ አሻራ ስኬት ሚስጥር ናይጄሪያ ወደ ኢትየጵያ በመምጣት ለመመልከት ከፍተኛ ተነሳሽነት እንደፈጠረባቸው ሚኒስትሩ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top