የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

9 Mons Ago 1049
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።

የክልሉ ምክር ቤት ጉባኤ ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን፤ በሚኖረው ቆይታም በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

ጉባኤው የባለፈው 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ረቂቅ ቃለጉባኤ በማፅደቅ የሚጀምር ሲሆን፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ምክር ቤት የ2016 በጀት ዓመት የባለፈው ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሏል።

ጉባኤው የምክር ቤቱን የአሠራርና የአባላት ሥነምግባር ደንብ ረቂቅ ደንብ እንዲሁም የአዲሱን ክልል አስፈፃሚ ተቋማት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን ልዩ ልዩ አዋጆች ላይ እንደሚመክርም ደሬቴድ ዘግቧል፡፡

 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top