በመዲናዋ በመሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ሲያደርሱ የተገኙ ከ 31 ሺህ በላይ ደንብ ተላላፊዎች ተቀጡ

1 Mon Ago 257
በመዲናዋ በመሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ሲያደርሱ የተገኙ ከ 31 ሺህ በላይ ደንብ ተላላፊዎች ተቀጡ

በአራት ቀን በተደረገ ቁጥጥር በተለያዩ ጥፋቶች ላይ የተገኙ ከ 31 ሺህ በላይ ደንብ ተላላፊዎች ተከሰው መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በቀንና በምሽት በተደረገ ቁጥጥር በመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ ጉዳት ያደረሱ፣ ከመጠን በላይ ጠጥተው የተገኙ፣ ካለ ደረጃ ሲያሽከረክሩ የተገኙ 31 ሺህ 893 አጥፊዎች ክስ ተመስርቶባቸው መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ከተቀጡት መካከል ለከተማዋ መልካም ገጽታ ያላበሱ እና ለትራፊክ ፍሰቱ መሳለጥ ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የመሰረተ ልማት አውታሮችና መንገዶቹን ለማስዋብ በውድ ዋጋ የተገዙ ስማርት ፖሎች፣ የተተከሉ ዘንባባዎች እና ሌሎች ተክሎች ላይ ጉዳት ያደረሱ አሽከርካሪዎች እንደሚገኙበት ተጠቅሷል።

በመሰረተ ልማት አውታሮቹ ላይ ጉዳት ያደረሱ አሽከርካሪዎችን፣ በተከለከሉ ቦታዎች ላይ ተሽከርካሪዎችን በማቆም ለፍስቱ መጨናነቅ ምክንያት የሆኑትን ጨምሮ ከኮሪደር ልማቱ ጋር ተያይዞ ውድ ዋጋ ያላቸው ስማርት የመንገድ ላይ ፖሎችን፣ ውብ ዘንባባዎችንና ሌሎች ልማቶች ላይ ጉዳት ያደረሱ አጥፊዎች የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ መደረጉንም ነው ፖሊስ ያስታወቀው፡፡

ሆን ብለው ጉዳት ያደረሱ ግለሰቦችም በወንጀል እንዲጠየቁ የማድረግ ስራ እንደተሰራ እና በቀንም ሆነ በምሽት የሚያከናውነውን የቁጥጥር ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top