የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የተለያዩ ሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረና የአመራር አቅምን በሚገነቡ ወቅታዊ ጉዳየች ዙሪያ ስልጠና ጀመሩ።
ስልጠናውን የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት እና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስጀምረዋል።
"የሕልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት" በሚል መሪ ሃሳብ እየተሰጠ በሚገኘው በዚህ ስልጠና፤ በሀገሪቱ የተመዘገቡ ውጤቶችን በላቀ ስኬት በመፈፀምና ተሞክሮን በማስፋት፣ ተግዳሮቶችን ወደ እድል በመቀየር የህዝብና የሀገርን ጥቅም ለማረጋገጥ በአመራሩ አቅም የሚያዝባቸው ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል።
የብልፅግና ፓርቲ ከህዝቡ ጋር በመሆን በፈጸማቸው ተግባራት የተጎናፀፋቸውን አንፀባራቂ ድሎች ይበልጥ በማጎልበት በቀጣይ የሚያከናውናቸው የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የጋራ አቋምና ዝግጁነት እንደሚፈጠርበትም ተመላክቷል፡፡
