የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከምን ጊዜውም በላይ በድንቅ ብቃት ላይ መሆኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ።
ሠራዊቱ ዘውትር ዝግጅት ያደርጋል ያሉት ኢታማዦር ሹሙ፣ "ሆኖም ዝግጅታችን በየአከባቢው ተሰንቅረው ላሉ ትናንሽ ታጣቂ ቡድኖች አይደለም፤ አቅማችን ከዚያ በላይ ነው" ሲሉ አክለዋል።

በሀገሪቱ በተለያዩ ክፍሎች ያሉ ታጣቂ ኃይሎች መንግሥት እያቀረበ ያለውን የሰላም ጥሪ እንዲቀበሉ እና ትጥቃቸውን በመፍታት ለሀገር ብልፅግና የበኩላቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።
ባለፉት ዓመታት በሀገሪቱ የፀና ሰላምን ለማምጣት መንግሥት በሆደ ሰፊነት በተለያዩ አማራጮች የሰላም ጥሪ ሲያቀርብ መቆየቱን አስታውሰዋል።

በራሔል አብደላ