Search

ግድባችንን ከመመረቅ የሚያስቀረን ምንም ምክንያት የለም፦ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት

ኢትዮጵያ ታላቁ ሕዳሴ ግድብን ከመመረቅ የሚያስቀራት ምንም ዓይነት ምክንያት እንደሌለ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ የተገነባው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ፣ የፊታችን መስከረም ወር ሕዝቡ ከመንሥግት ጋር በመሆን የምርቃት ሪቫኑን ይቆርጡታል ሲሉ የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ማስተባባሪያ ጽሕፈት ቤት ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ፍቅርተ ተዓምር ገለጹ።
 
 
የሕዳሴ ግድብ በመንግሥት እና በሕዝቡ መዋጮ የተገነባ ፕሮጀክት ነው ያሉት ምክትል ዋና ሥራዋ አስፈፃሚዋ፣ ማንም አካል ተነሥቶ እኔ ነኝ የሠራሁት ቢል ምንም ማድረግ አይችልም ብለዋል።
በኢትዮጵያውያን ብርቱ ርብርብ የተገነባውን ግድባችንን ከመመረቅ የሚያስቀረን አንዳችም ምክንያት የለም ሲሉም ገልጸዋል።
ላለፉት 14 ዓመታት ለግድቡ ግንባታ ምንም ዓይነት ገንዘብ ከውጭ ብድር እና ዕርዳታ እንዳልተደረገ ሲገለጽ መቆዩቱንም አስታውሰዋል።
ለግድቡ የሚደረገው ድጋፍ ሪቫኑ እስቀሚቆረጥበት ዕለት ድረስ ይቀጥላል ያሉት ወይዘሮ ፍቅርተ፣ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ብዙ ቦንድ እየተሸጠ ስለመሆኑም ገልጸዋል።

 

በሃይማኖት ከበደ