Search

ታርጫ ስቱዲዮ - የኢቢሲ ተጨማሪ የይዘት ምንጭ ተመርቆ ተከፈተ 🔥

ኢቢሲ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ታርጫ ከተማ ተጨማሪ የይዘት ምንጭ የሆነው አዲስ ስቱዲዮ በክልሉ ርእሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በይፋ ተመርቆ ተከፍቷል።
በምርቃት ስነ-ስርአቱ ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፣ የኢቢሲ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጌትነት ታደሰ እና የብልጽግና ፓርቲ ዓለም አቀፍና የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታዳሚ ሆነዋል።