Search

የተመድ ምግብ ሥርዓት ጉባኤ ተሳታፊዎች ኢትዮጵያ በምግብ ትራንስፎርሜሽን ያከናወነቻቸውን ሥራዎችን ይጎበኛሉ

አዲስ አበባ ሁለተኛውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ ከዛሬ ጀመሮ  ታስተናገዳለች።

የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሐመድ እና የበርካታ ዓለም ሀገራት ተወካዮች በጉባኤው ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጉባኤው የዓለም ምግብ ሥርዓትን ከዘላቂ ልማት ግቦች ጋር በማስተሳሰር ለውጥ የማምጣት ጥረት አካል ነው።

በዛሬው ዕለት የሚካሄደው የጉባዔ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት የ"ተግባር ቀን'' የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።

የጉባኤው ተሳታፊዎች በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያ በምግብ ትራንስፎርሜሽን እያከናወነቻቸው የሚገኙ ሥራዎችን ይጎበኛሉ።

በቢሾፍቱ፣ በአዳማ፣ በሞጆ፣ በመልካሳ እና በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የልማት ሥራዎች የሚጎበኙ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በምግብ ሥርዓት የልማት ሥራዎች ያከናወነቻቸው ጉልህ ተግባራትን በስፋት ለዓለም የምታሳይበት አጋጣሚም ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል።

#ebcdotstream #UN #unfss2025 #Ethiopia