Search

ኢትዮጵያ በምግብ ሥርዓት ማሻሻያ ላይ ለዓለም መፍትሄ ለማምጣት ትክክለኛዋ ሀገር ነች - ሌና ሳቬሊ

አዲስ አበባ መገኘታችን ታሪካዊ ነው ያሉት የተመድ ምግብ ሥርዓት ማስተባበሪያ ማዕከል /ዳይሬክተር ሌና ሳቬሊ በምግብ ሥርዓት ማሻሻያ ላይ ለዓለም መፍትሄ ለማምጣት ትክክለኛው ቦታ ላይ ነው ያለነው ብለዋል

ኢትዮጵያ የምግብ ሥርዓቷን ለማሻሻል እየሰራችው ያለው ሥራም የሚደነቅ ነው ሲሉ ለኢቢሲ ገለፀዋል።

ይህንን ከአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ሥራዎች ጋር አስተሳስራ መስራቷ ደግሞ የሚያስመግናት ነው ብለዋል።

"ጉባዔው በውቢቷ አዲስ አበባ መዘጋጀቱ በጣም ደስ ያሰኛል፤ አዲስ አበባ በትክክልም የአፍሪካ መዲና ነች" ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የምግብ ሥርዓትን ለማሻሻል ያከናወነቻቸው ስራዎች ለሌሎች አገራት ዓርአያ እንደሚሆኑ አስረድተዋል።

በጉባዔው ከሚነሱ ሃሳቦች ውጤታማ ሃሳብ እንጠብቃለን ያሉት ምክልትል ዳይሬክተሯ፤ ጉባዔውም ስኬታማ እንደሚሆን ይጠበቃል ሲሉ ገልጸዋል።

#EBC #ebcdotstream #UN #unfss2025 #Ethiopia