Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኬንያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኬንያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ጋር ኢትዮጵያ በጋራ ከምታዘጋጀው ከሁለተኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓቶች ጉባኤ አስቀድሞ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፥ ውይይቱ በሁለትዮሽ ግንኙነቶች እና የጋራ ፍላጎት በሆኑ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር ብለዋል።