ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ባለፉት 4 ዓመታት በርካታ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ትገኛለች።
ይህንኑ አስመልክቶ ኢቢሲ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 የኢትዮጵያ የምግብ ሥርዓት ሽግግር እና ኒውትሪሽን ፕሮግራም፤ የጤናማ አመጋገብ እና ሥርዓተ ምግብ ክላስተር አስተባባሪ የሆኑትን ሀምቢሳ ሙለታ (ዶ/ር) አነጋግሯል።
ኢትዮጵያ በምግብ እራስን ለመቻል ካከናወነቻቸው ተግባራት መካከል የበጋ ስንዴ ምርት አንዱ ሲሆን፤ በሀገር ውስጥ በሚመረት ምርት ከውጪ የሚገቡትን ለመተካት ለሚደረገው ጥረት አንዱ ምሳሌ እንደሆነ ሀምቢሳ ሙለታ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
የእንስሳት ተዋፅኦ የሆኑ የሌማት ትሩፋት ውጤቶችን በማምረት ማህበረሰቡ ምግቦች ስብጥራቸው ተጠብቆ እንዲመገብ፤ ብሎም ምርቶች በአግባቡ በማድረስ ሰዋ ተኮር የሆኑ ተግባራት መከናወናቸውንም ነው ያነሱት።
ከእነዚህም መካከል የትምህርት ቤት ምገባ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህፃናት ትምህርታቸው ላይ ትኩረት አድረገው እንዲማሩ ከማድረግ ባለፈ፤ ጤንነታቸው ተጠብቆ ትምህርታቸው ሳይቋረጥ እንዲማሩ ማድረግ ያስቻለ ተግባር መከናወኑንም ነው የገለፁት።
ከተጀመረ 10 ዓመታት ያስቆጠረው የሰቆጣ ቃል ኪዳን በዚህ ዓመት ብቻ፤ በሁሉም ክልሎች በ334 ወረዳዎች ተደራሽ በመሆን በርካታ ማኅበረሰቦችን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶች ዜጎች የምግብ ዋስትናቸውን የሚያረጋግጡበት ዋነኛ መንገዶች ናቸውም ብለዋል ሀምቢሳ ሙለታ (ዶ/ር)።
በንፍታሌም እንግዳወርቅ