የዛሬው ዕለት መቻላችንን ደግመን ለዓለም የምናሳይበት ዕለት ነው ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ገለጹ።
ሚኒስትር ዴኤታው በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ-ግብሩ መጀመሩን አብስረዋል።
በአንድ ጀምበር በርካታ ችግኞችን በመትከል እስከዛሬ የራሳችንን ክብረ ወሰን ስናሻሽል መጥተናል ያሉት አቶ ተስፋሁን፣ ዛሬም አዲስ ታሪክ ጽፈን ለዓለም ለማሳየት ተዘጋጅተናል ብለዋል።
ኢትዮጵያውያን የዛሬ ዓመት 617 ሚሊዮን በመትከል ክብረ ወሰን መያዛቸውን አስታውሰው፣ ዛሬም 700 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የራሳቸውን ክብረ ወሰን የሚያሻሽሉበት ዕለት እንደሆነ ተናግረዋል።
ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል ለዚህ ዝግጁ መሆኑንም አውስተዋል።
ችግኞችን የምንተክለው የአየር ንብረት ለውጥን ለመከከላከል፣ የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ፣ ግድቦቻችንን ከደለል ለመጠበቅ እንዲሁም ሌሎች በርካታ ጠቀሜታዎችን ለማግኘት መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው ጠቅሰዋል።
ዛሬ በሁሉም ወጥቶ ችግኝ መተከል በሚቻልባቸው ቦታዎች ሁሉ እንዲተክል እና ለእናት ሀገር ትንሽ የማበርከት ዕድሉን እንዲጠቀም ጥሪ አቅርበዋል።
በለሚ ታደሰ
#Green_Legacy #700_Million_Seedlings #Plant_For_Ethiopia #My_Tree_My_Future #Ethiopia_Plants_Tomorrow