Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ-ግብር በይፋ አስጀመሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ-ግብር በጅማ አባጅፋር ቤተመንግሥት በይፋ አስጀምረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመርሐ-ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ባደረጉት ንግግር በአንድ ጀምብር 700 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል እጅግ ትልቁ እመርታ እና በዓለም ትልቁ የአንድ ቀን ተከላ ውጤት ነው ብለዋል።
ይህ ኢትዮጵያ ትላልቅ ነገር አልማ እና አቅዳ፣ ሕዝቦቿን አስተባብራ ማሳካት እንደምትችል ትልቅ ማሳያ እንደሆነም ጠቁመዋል።
"እኛ እስከዛሬ ይህንን ሁሉ ችግኝ መትከል የቻልነው ሀብታም ስለሆንን ሳይሆን ሀብታም ልብ ያላቸው ዜጎች ስላለን ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው።
እኛ ኢትዮጵያውያን አርቆ ማየት እና በጋራ መቆም እንደምንችል፤ በልፋት እና በድካም ትርፋማ መሆን እንደምንችል ለዓለም የምናሳይ ሕዝቦች ነን ብለዋል።
ልክ እንደ ሕዳሴው በአረንጓዴ ዐሻራውም ስኬታማ ሆነናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ “የኢትዮጵያ ታሪክ ይቀየራል፤ የዚያ ታሪክ እጥፋት አካል መሆን መታደል ነውና እንኳን ደስ አላችሁ” ሲሉ አክለዋል። ለዚህ ስኬት አስተዋፅኦ ላደረጉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በዮናስ በድሉ