ታላቁ የህዳሴ ግድብ ያከሸፈው ሴራ

1 Day Ago 245
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ያከሸፈው ሴራ
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ወደ መጠናቀቅ መቃረብ፤ በጥቅም ተደልለው የጸጥታ ችግር እንዲሁም ሌሎች ሳንካዎችን የሚፈጥሩ የውስጥ ተላላኪዎችን ሴራ ያከሸፈ መሆኑን አንጋፋው የታሪክ እና ፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ አለማየሁ አረዳ (ዶ/ር) ተናገሩ።
አለማየሁ አረዳ (ዶ/ር) በኢቢሲ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ወቅታዊ ውይይት ላይ በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት፤ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ውስብስብ የዲፕሎማሲ ፈተናዎችን በብልሀት እና አንድነት አልፎ ወደ መጠናቀቅ መቃረብ ኢትዮጵያ ትልቅ ድል እንድታስመዘግብ አስችሏታል።
ከዓባይ አንዲት ጠብታ ውሀ መንካት አትችሉም የሚለውን መሰረተ ቢስ ዛቻ መና መሆኑን ኢትዮጵያውያን በራሳቸው አቅም ገንብተው ያሳዩበት መሆኑንም ነው አለማየሁ አረዳ (ዶ/ር) ያነሱት።
የዓባይን ወንዝ መጠቀም ግብፅን መጉዳት ነው ይህም አረቡን ማህበረሰብ መተንኮስ ነው የሚል የአሉታዊ አስተሳሰብ አቋምም የከሸፈበት መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካውያን የነጻነት ተጋድሎ የነበራትን ፊት አውራሪነት በኢኮኖሚው መስክም ትደግመዋለች በሚል ስጋት የሚገባቸውን ቅኝ ገዢዎች ስውር ጥርነፋ ድል የነሳንበት ነውም ብለዋል አለማየሁ አረዳ (ዶ/ር)።
ግብፅ ከምትከፋ ኢትዮጵያ ትራብ የሚለውን የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ያልተገባ ጫናም ኢትዮጵያ በራሷ አቅም ሰርታ ውድቅ አድርጋዋለች ሲሉ ተናግረዋል።
በቤተልሔም ገረመው

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top